Friday, August 26, 2011

(ሰበር ዜና) አቡነ አብርሃምና አቡነ ኤውስጣቴዎስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተጠየቁ

መኖሪያቸውን አሜሪካ ያደረጉ አባቶች የአቡነ አብርሃም እና የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከቦታቸው መነሳት ዋነኛ አጀንዳ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2003 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡ ከስብሰባውም አጀንዳዎች ዋነኛው በዋሽንግተን እና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የሎስ አንጀለስ ና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ጉዳይ ይሆናል፡፡ ከቅርብ ጊዜ በፊት በቀንደኛ የተሐድሶ አራማጅነታቸው የሚታወቁትን ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ልዩ ሹም” በማለት በቅዱስ ፓትርያሪኩ መሾማቸው ሲሆን ውሳኔውን እና ሹመቱን በመቃወም ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት የተቃውሞ ድብዳቤ መጻፋቸው ነው፡፡ የተቃውሞው ይዘት ቃለ አዋዲው እና ቀኖና ቤተክርስቲያን ተጥሷል የሚል ሲሆን በአንድ ሀገረ ስብከት የሁሉም የበላይ ሊቀ ጳጳሱ መሆን ሲገባው ከሊቀ ጳጳሱ በላይ “ልዩ ሹም” መሾም ተገቢ አይደለም ይላሉ፡፡ በዚህ ተቃውሞም የተነሳ ዛሬ በሚደረገው የቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ሁለቱንም ሊቃነ ጳጳሳት ከቦታቸው በማንሳት ወደ አገር ቤት አንዲሄዱ ሊወሰን እንደሚችል ቤተ ክርስቲያኒቱ ገለጸች።

1 comment:

  1. አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በአለም እየዞሩ እንዳስተማሩ ሁሉ እነዚህም አባቶች እንዲሁ ማድረግ አለባቸው። ቅዱስ ሲኖዶስን ማክበር አለባቸውና ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ሕዝባቸውን ያገልግሉ ከዚህም አንድ አይነት ሕዝብ ነውና የሚያገለግሉት ስለዚህ ቢመለሱም መልካም ስለሆነ ይህ ጠብ አያስፈልገውም እላለሁ አለበለዚያ ግን የግል ጥቅም ፍለጋ በቤተ ክርስቲያን ስም ሰበብ እንዳይሆን እፈራለሁ።

    ReplyDelete