Tuesday, August 30, 2011

‹‹ቤተክርስትያኒቷ ትዘጋ›› የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም››

ጊዜው ወርሀ ክረምት ነው :: የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፆመ ፍልሰታ ወቅት ሲሆን በቤተክርስትያናችን ህግና ስርዓት መሰረት ይህ ጊዜ ዲያቆናት ፤ ካህናት መነኮሳት ፤ ጳጳሳት እና ምእመናን ለሐዋርያት የተገለፅሽላቸው እናታችን ለእኛም በምህረት አትለይን እያሉ በፆም ፤ በፀሎት ፤ በስግደት የሚለምኑበት ጊዜ ነው፡፡

ቦታው በሐረር መንገድ አዋሽ ሰባትን አልፈው ካለው የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያ ትንሽ ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ከአሰቦት ገዳም መገንጠያ ሳይደርስ ከዋናው አስፋልት አንድ ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ሲሆን የቦታው ስም ቦርደዴ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቤተክርስትያን የሚገኝበት ቦታ ላይ ከ30 የማይበልጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሲገኙ በቁጥር ከ40 እና ከ50 እጥፍ ልቀው የሚገኙት ግን ሙስሊም ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ ይህ ቦታ ለአንድ አፍታም ቢሆን ከነገር እና ከትንኮሳ እፎይ ያለበት ጊዜ የለም፡፡ ቦታ ድረስ ሄጄ በተመለከትኩበት ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ያለው የሙቀት መጠን ክረምት ሳይል በጋ ከ40 ድግሪ በላይ ስለሆነ ቆሞ ማስቀደስ እንደ እግዚሐብሔር መልካም ፍቃድ ፤ ምህረት ፤ ቸርነት እንጂ እንደ እኛ ብርታትና ጥንካሬ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡
ቤተክርስትያኒቷ አካባቢ ያሉት ምዕመና ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብ እና ንዋየ ቅዱሳትን ማሟላት አቅሙ ስለሌላቸው ይህ ችግር የቀን ተቀን የውስጥ ችግር ችግራቸው ሆኖ አሁንም አሉ ፡፡ የባሰ አታም ነውና  አንድ ጊዜ ቅዳሴ ላይ ወንጌል ለማንበብ ጧፍ አልቆ በኩራዝ የተጠቀሙበት ጊዜም ነበር ፡፡
በአካባቢው የሚገኙ ከአክራሪ ወገን የሚመደቡት የእስልምና ተከታዮች በአካባቢው ላይ ለ24 ሰዓት ያህል ከ4 በሚበልጡ መስኪዶቻቸውን ድምፅ ማውጫ Speaker ወደ ቤተክርስትያን አዙረው ‹‹አላህ ዋክበር›› በሚሉበት ሁኔታ ላይ ምንም ጥያቄ ያላቀረቡት በአካባቢው የሚገኙ  ክርስትያኖች በዓመት አንድ ጊዜ ለ16 ቀናት ብቻ ያለውን የሱባኤ ጊዜ ለሊት ሰዓታት እና ኪዳኑ ፤ ጠዋት ትርጓሜው እና ስብከቱ ፤ ከሰዓት ቅዳሴው ረበሸን ብለው ቤተክርስትያኒቷ እንድትዘጋላቸው  ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸውን አረጋግጠናል፡፡ ይህን ጥያቄ የመስተዳድሩ  ሃላፊ ከሰማ በኋላ ለሚቀጥለው ቀን የቀጠራቸው ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ሲመጡ ምንም ምላሽ ስላላገኙ ሓላፊውን በኃይል ከቢሮ ያባረሩት ሲሆን ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው የክልሉ መንግስ ጋር እንደደረሰ ፤ አካባቢው ላይ የሚገኙ ክርስትያኖች ጉዳዩን ወደ ፊደራል መንግስት የወሰዱት ሲሆን መንግስት የዛኑ ቀን ማታ አካባቢው ላይ የሚገኙ ፌደራል ፖሊሶች ማታ 3፡00 አካባቢ ወደ አካባቢው በፓትሮል በመምጣት ይህን ጥያቄ የጠየቁትን ሰዎች ግማሽ ያህሉን ለቅመው ወስደው ወደ እስር ቤት የከተቷቸው  ሲሆን የተቀሩትን ግን ሸሽተው አምልጠዋል፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ ሁኔታውን በጥቂቱ ያረጋጋ ሲሆን ፡፡ በአሁኑ ወቅት አካባቢው በፊደራል ፖሊስ  እየተጠበቀ ይገኛል::

እኛ በአሁኑ ሰዓት እንትና 18 ገፅ ወቀሳ ፃፈ ፤ ያኛው ሰባኪ አውደ ምህረት ላይ እንዳይቆም ተከለከለ ፤ በዚህ መፅሄት ላይ እንትና መልስ ሰጠ ፤ አንዱ ይቅርታ አለ ሌላኛው ይቅርታ ተቀበለ እያልን ስራ መስራት በሚገባን ወቅት ወሬ ስናራግብ ለቤተክርስትያን መሆን በሚገባን ሰዓት ጊዜያችንን እና አቅማችንን አልባሌ ቦታ ላይ በማዋልና ትርፍ የሌለው ስራ በመስት ላይ እንገኛለን፡፡

አሁንም ጊዜው አልረፈደም ስለ ጥቂት ሰዎች ማውራታችንን አቁመን ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ዘብ እንቁም ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ይህን የጠየቁ ሰዎች ነገ ምን ማድረግ እንደሚያስቡ ለማስረዳት መምህር ሊያሻን አይገባም፡፡

በዚች ምድር ላይ የምንቆየው እንደ ማቱሳላ 969 ዓመት አለመሆኑን አውቀን በኖርንበት፤በምንኖርበት  ጊዜ ሁሉ ከቤተክርስትያን ጎን ለመቆም ያብቃል፡፡

(ከአምደ ሃይማኖት)

ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም
‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ››

2 comments:

 1. እንደምን አለህ ወንድሜ …ይህን ፅሁፍ ስላወጣህው ደስ ብሎኛል እኔ www.andadirgen.blogspot.com የብሎጉ ባለቤት ነኝ ይህን ፅኁፍ ያሰፈርኩት እኔ ነኝ ነገር ግን አንተ በራህ ብሎግ ስም አውጥተህዋ ቢያንስ ከታች ያገኝህበትን ብሎግ ብትጠቅስ ጥሩ ነው ፡፡ ራስህ የፃፍከውን ፅኁፍ በራስህ ስም ወይም በብሎጉ ስም አውጣ የራስህ ያልሆነውን ደግሞ ያገኝህበትን ቦታ ጥቀስ ፡፡ ለማንኛውም አንተም እኔም የአንዲት ተዋህዶ ልጆች ስለሆንን አላማችንም ስለሚያመሳስለን አብሬ ለመስራት ቃል እገባልሀለሁ……
  አንድ አድርገኝ

  ReplyDelete
 2. I am TGM the member of andadrigen
  ere shame atafrim ende anten bilo amdehaymanot . post sidereg source yithekesal kalawekih malet neew endezih aynet lebnet thiru aydelem andu belefaw fithith bilo ende ras mawthat dirkina neew siletsafkew neger further bititheyek melis endeleleh ene awkalehu le ewnet be ewnet yekome enji endezih aynet ema betekirstian mech athach bezih yaltamene blog minim tesfa ayithalibetim silezih lerasih tamagn hun. zirfiya yibka the owner of this post is www.andadrigen.blogspot.com period.
  lelochum tsihufoch yante aydelum ena pleace be ur self wey shame besinitu likathel alech ....................

  ReplyDelete